Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia 1994
Political Rights and Association
  • English
    Every person has the right to freedom of association for any cause or purpose. … (Art. 31)
  • Amharic
    ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማኅበር የመደራጀት መብት አለው፡፡ … (አንቀጽ 31)
Political Rights and Association
  • English

    3. The historical legacy of inequality and discrimination suffered by women in Ethiopia taken into account, women, in order to remedy this legacy, are entitled to affirmative measures. The purpose of such measures shall be to provide special attention to women so as to enable them to compete and participate on the basis of equality with men in political, social and economic life as well as in public and private institutions.
    … (Art. 35)
  • Amharic

    3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
    … (አንቀጽ 35)
Political Rights and Association
  • English
    1. Every Ethiopian national, without any discrimination based on colour, race, nation, nationality, sex, language, religion, political or other opinion or other status, has the following rights:
    a. To take part in the conduct of public affairs, directly and through freely chosen representatives;
    b. On the attainment of 18 years of age, to vote in accordance with law;
    c. To vote and to be elected at periodic elections to any office at any level of government; elections shall be by universal and equal suffrage and shall be held by secret ballot, guaranteeing the free expression of the will of the electors.
    2. The right of everyone to be a member of his own will in a political organization, labour union, trade organization, or employers' or professional association shall be respected if he or she meets the special and general requirements stipulated by such organization.
    3. Elections to positions of responsibility within any of the organizations referred to under sub-Article 2 of this Article shall be conducted in a free and democratic manner.
    4. The provisions of sub-Articles 2 and 3 of this Article shall apply to civic organizations which significantly affect the public interest. (Art. 38)
  • Amharic
    1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለከካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት የሚከተሉት መብቶች አሉት፤
    ሀ/ በቀጥታ እና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በሕዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ፣
    ለ/ ዕድሜው 18 ዓመት ሲሞላ በሕግ መሰረት የመምረጥ ፣
    ሐ/ በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ፡፡ ምርጫው ሁሉ አቀፍ፣ በሁሉም እኩልነት ላይ የተመሰረተና በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ መራጩ ፈቃዱን በነጻነት የሚገልጽበት ዋስትና የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡
    2. በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሠራተኞች፣ በንግድ፣ በአሠሪዎችና በሙያ ማኅበራት ለተሳትፎ ድርጅቱ የሚጠይቀውን ጠቅላላና ልዩ የአባልነት መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ሰው በፍላጐቱ አባል የመሆን መብቱ የተከበረ መሆን አለበት፡፡
    3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 በተመለከቱት ድርጅቶች ውስጥ ለኃላፊነት ቦታዎች የሚካሄዱ ምርጫዎች ነጻና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ይፈጸማሉ፡፡
    4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 ድንጋጌዎች የሕዝብን ጥቅም ሰፋ ባለ ሁኔታ የሚነኩ እስከሆነ ድረስ በሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ (አንቀጽ 38)
Electoral Bodies
  • English
    1. There shall be established a National Election Board independent of any influence, to conduct in an impartial manner free and fair election in Federal and State constituencies.
    … (Art. 102)
  • Amharic
    1. በፌዴራልና በክልል የምርጫ ክልሎች ነጻና ትክክለኛ ምርጫ በገለለተኝነት እንዲያካሂድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡
    … (አንቀጽ 102)
Head of State
  • English
    The President of the Federal Democratic Republic of Ethiopia is the Head of State. (Art. 69)
  • Amharic
    ኘሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው፡፡ (አንቀጽ 69)
Head of State
  • English
    1. The House of Peoples' Representatives shall nominate the candidate for President.
    2. The nominee shall be elected President if a joint session of the House of Peoples' Representatives and the House of the Federation approves his candidacy by a two-thirds majority vote.
    … (Art. 70)
  • Amharic
    1. ለኘሬዚዳንትነት እጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡
    2. የቀረበው እጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ኘሬዚዳንት ይሆናል፡፡
    … (አንቀጽ 70)
Government
  • English
    1. The highest executive powers of the Federal Government are vested in the Prime Minister and in the Council of Ministers.
    … (Art. 72)
  • Amharic
    1. የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የአስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው፡፡
    … (አንቀጽ 72)
Government
  • English
    1. The Prime Minister shall be elected from among members of the House of Peoples' Representatives.
    2. Power of Government shall be assumed by the political party or a coalition of political parties that constitutes a majority in the House of Peoples' Representatives. (Art. 73)
  • Amharic
    1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል፡፡
    2. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው የፖለቲካ ድርጅት ወይም ያገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች የመንግሥት ሥልጣን ይረከባል/ይረከባሉ፡፡ (አንቀጽ 73)
Government
  • English

    2. The Prime Minister shall submit for approval to the House of Peoples' Representatives nominees for ministerial posts from among members of the two Houses or from among persons who are not members of either House and possess the required qualifications.
    … (Art. 74)
  • Amharic

    2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለሥራው ብቃት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያጸድቃል፡፡
    … (አንቀጽ 74)
Government
  • English
    1. The Council of Ministers comprises the Prime Minister, the Deputy Prime Minister, Ministers and other members as may be determined by law.
    … (Art. 76)
  • Amharic
    1. የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ሚኒስትሮችና በሕግ በሚወሰን መሰረት ሌሎች አባሎች የሚገኙበት ምክር ቤት ነው፡፡
    … (አንቀጽ 76)
Legislature
  • English
    There shall be two Federal Houses: The House of Peoples' Representatives and the House of the Federation. (Art. 53)
  • Amharic
    የፌዴራሉ መንግሥት ሁለት ምክር ቤቶች ይኖሩታል፤ እነዚህም የሕዝብተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ናቸው፡፡ (አንቀጽ 53)
Legislature
  • English
    1. Members of the House of Peoples' Representatives shall be elected by the People for a term of five years on the basis of universal suffrage and by direct, free and fair elections held by secret ballot.
    2. Members of the House shall be elected from candidates in each electoral district by a plurality of the votes cast. Provisions shall be made by law for special representation for minority Nationalities and Peoples.
    3. Members of the House, on the basis of population and special representation of minority Nationalities and Peoples, shall not exceed 550; of these, minority Nationalities and Peoples shall have at least 20 seats. Particulars shall be determined by law.
    … (Art. 54)
  • Amharic
    1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ሁሉ አቀፍ፣ ነጻ ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ፡፡
    2. የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የተለየ ውክልና ያሰፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ይሆናሉ፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
    3. የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው አናሳ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ 550 የማይበልጥ ሆኖ ከዚህ ውስጥ አናሳ ብሔረሰቦች 20 የማያንስ መቀመጫ ይኖራቸዋል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይደነግጋል፡፡
    … (አንቀጽ 54)
Legislature
  • English
    1. The House of the Federation is composed of representatives of Nations, Nationalities and Peoples.
    2. Each Nation, Nationality and People shall be represented in the House of the Federation by at least one member. Each Nation or Nationality shall be represented by one additional representative for each one million of its population.
    3. Members of the House of the Federation shall be elected by the State Councils. The State Councils may themselves elect representatives to the House of the Federation, or they may hold elections to have the representatives elected by the people directly. (Art. 61)
  • Amharic
    1. የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፌዴራሉ መንግሥት አባል ክልሎች የሚገኙ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኩዋቸው አባላት የሚወከሉበት ምክር ቤት ነው፡፡
    2. እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ቢያንስ አንድ ተወካይ ይኖረዋል፤በተጨማሪም የብሔር ወይም ብሔረሰቡ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ተጨማሪ ወኪል ይኖረዋል፡፡
    3. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በክልል ምክር ቤቶች ይመረጣሉ፤ የክልል ምክር ቤቶች በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሕዝብ እንዲመረጡ በማድረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እንዲወከሉ ያደርጋሉ፡፡ (አንቀጽ 61)
1

Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia 1994 (English). According to Art. 106: “The Amharic version of this Constitution shall have final legal authority.” There are discrepancies in the content of the English and Amharic texts.

2

Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia 1994 (Amharic). Copy obtained from the Ministry of Justice, Ethiopia.

Links to all sites last visited 6 March 2024
3
Chapter Three on Fundamental Rights and Freedoms.
4
Chapter Three on Fundamental Rights and Freedoms.
5
Chapter Three on Fundamental Rights and Freedoms.