SEARCH DATABASE
The Global Gender Equality Constitutional Database is a repository of gender equality related provisions in 194 constitutions from around the world. The Database was updated in partnership with the International Bar Association's Human Rights Institute (IBAHRI) and with support from the Swedish International Development Agency (SIDA) and the Government of Japan. Experience its wealth and depth of information by starting your search now.
Status of International Law
- English…
2. The fundamental rights and freedoms specified in this Chapter5 shall be interpreted in a manner conforming to the principles of the Universal Declaration of Human Rights, International Covenants on Human Rights and International instruments adopted by Ethiopia. (Art. 13) - Amharic…
2. በዚህ ምዕራፍ የተዘረዘሩት መሠረታዊ የመብቶችና የነጻነቶች ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሰነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ ይተረጐማል፡፡ (አንቀጽ 13)
Status of International Law
- English…
4. All international agreements ratified by Ethiopia are an integral part of the law of the land. (Art. 9) - Amharic…
4. ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል ናቸው፡፡ (አንቀጽ 9)
Women’s Rights
- English1. Women shall, in the enjoyment of rights and protections provided for by this Constitution, have equal right with men.
2. Women have equal rights with men in marriage as prescribed by this Constitution.
3. The historical legacy of inequality and discrimination suffered by women in Ethiopia taken into account, women, in order to remedy this legacy, are entitled to affirmative measures. The purpose of such measures shall be to provide special attention to women so as to enable them to compete and participate on the basis of equality with men in political, social and economic life as well as in public and private institutions.
4. The State shall enforce the right of women to eliminate the influences of harmful customs. Laws, customs and practices that oppress or cause bodily or mental harm to women are prohibited.
5. a. Women have the right to maternity leave with full pay. The duration of maternity leave shall be determined by law taking into account the nature of the work, the health of the mother and the well-being of the child and family.
b. Maternity leave may, in accordance with the provisions of law, include prenatal leave with full pay.
6. Women have the right to full consultation in the formulation of national development policies, the designing and execution of projects, and particularly in the case of projects affecting the interests of women.
7. Women have the right to acquire, administer, control, use and transfer property. In particular, they have equal rights with men with respect to use, transfer, administration and control of land. They shall also enjoy equal treatment in the inheritance of property.
8. Women shall have a right to equality in employment, promotion, pay, and the transfer of pension entitlements.
9. To prevent harm arising from pregnancy and childbirth and in order to safeguard their health, women have the right of access to family planning education, information and capacity. (Art. 35) - Amharic1. ሴቶች ይህ ሕገ መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
2. ሴቶች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
4. ሴቶች ከጐጂ ባሕል ተጽዕኖ የመላቀቅ መብታቸውን መንግሥት ማስከበር አለበት፡፡ ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ወይም በአዕምሮአቸው ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሕጐች፣ ወጐችና ልማዶች የተከለከሉ ናቸው፡፡
5. ሀ/ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው፡፡ የወሊድ ፈቃድ ርዝመት ሴቷ የምትሠራውን ሥራ ሁኔታ፣የሴቷን ጤንነት፣ የሕጻኑንና የቤተሰቡን ደህንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕግ ይወሰናል፡፡
ለ/ የወሊድ ፈቃድ በሕግ በሚወሰነው መሰረት ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የሚሰጥ የእርግዝና ፈቃድን ሊጨምር ይችላል፡፡
6. ሴቶች በብሔራዊ የልማት ፖሊሲዎች ዕቅድና በኘሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም፣በተለይ የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ኘሮጀክቶች ሐሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው፡፡
7. ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብት አላቸው፡፡ በተለይም መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡ እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት አላቸው፡፡
8. ሴቶች የቅጥር፣ የሥራ እድገት፣ የእኩል ክፍያና ጡረታን የማስተላለፍ እኩል መብት አላቸው፡፡
9. ሴቶች በእርግዝናና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከልና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣ መረጃ እና አቅም የማግኘት መብት አላቸው፡፡ (አንቀጽ 35)
Jurisdiction and Access
- English1. The House has the power to interpret the Constitution.
… (Art. 62) - Amharic1. ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጐም ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
… (አንቀጽ 62)
Jurisdiction and Access
- English
1. The Council of Constitutional Inquiry shall have powers to investigate constitutional disputes. Should the Council, upon consideration of the matter, find it necessary to interpret the Constitution, it shall submit its recommendations thereon to the House of the Federation.
2. Where any Federal or State law is contested as being unconstitutional and such a dispute is submitted to it by any court or interested party, the Council shall consider the matter and submit it to the House of the Federation for a final decision.
3. When issues of constitutional interpretation arise in the courts, the Council shall:
a. Remand the case to the concerned court if it finds there is no need for constitutional interpretation; the interested party, if dissatisfied with the decision of the Council, may appeal to the House of the Federation.
b. Submit its recommendations to the House of the Federation for a final decision if it believes there is a need for constitutional interpretation.
… (Art. 84) - Amharic
1. የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ በሚያደርገው ማጣራት መሰረት ሕገ መንግሥቱ መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፡፡
2. በፌዴራሉ መንግሥትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጐች ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳና ጉዳዩም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፡፡
3. በፍርድ ቤቶች የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ፣
ሀ/ ሕገ መንግሥቱን መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ይመልሳል፤ በአጣሪ ጉባኤው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡
ለ/ የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሳኔ ያቀርባል፡፡
… (አንቀጽ 84)
Jurisdiction and Access
- English1. All constitutional disputes shall be decided by the House of the Federation.
2. The House of the Federation shall, within thirty days of receipt, decide a constitutional dispute submitted to it by the Council of Constitutional Inquiry. (Art. 83) - Amharic1. የሕገ መንግሥታዊ ክርክር ጉዳይ ሲነሳ በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ውሳኔ ያገኛል፡፡2. የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በሚያቀርብለት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ላይ በሠላሣ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ (አንቀጽ 83)
Obligations of the State
- English1. All Federal and State legislative, executive and judicial organs at all levels shall have the responsibility and duty to respect and enforce the provisions of this Chapter3.
2. The fundamental rights and freedoms specified in this Chapter shall be interpreted in a manner conforming to the principles of the Universal Declaration of Human Rights, International Covenants on Human Rights and international instruments adopted by Ethiopia. (Art. 13) - Amharic1. በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል መንግሥትና የክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች በዚህ ምዕራፍ የተካተቱን ድንጋጌዎች የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው፡፡
2. በዚህ ምዕራፍ የተዘረዘሩት መሠረታዊ የመብቶችና የነጻነቶች ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሰነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ ይተረጐማል፡፡ (አንቀጽ 13)
Obligations of the State
- English1. Human rights and freedoms, emanating from the nature of mankind, are inviolable and inalienable.
2. Human and democratic rights of citizens and peoples shall be respected. (Art. 10) - Amharic1. ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፣ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡
2. የዜጐች እና የሕዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ፡፡ (አንቀጽ 10)
Obligations of the State
- EnglishWe, the Nations, Nationalities and Peoples of Ethiopia: …
Firmly convinced that the fulfillment of this objective requires full respect of individual and people’s fundamental freedoms and rights, to live together on the basis of equality and without any sexual, religious or cultural discrimination;
… (Preamble) - Amharicእኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ …
ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስ፣ የግለሰብና የብሔር/ብሔረሰብ መሰረታዊ መብቶች መከበራቸው፣ የጾታ እኩልነት መረጋገጡ፣ ባሕሎችና ሃይማኖቶች ካለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ የማድረጉ አስፈላጊነት ጽኑ እምነታችን በመሆኑ
… (መግቢያ)
Obligations of the State
- English1. The House of Peoples' Representatives shall have the power of legislation in all matters assigned by this Constitution to Federal jurisdiction.
…
7. It shall determine the organization of national defence, public security, and a national police force. If the conduct of these forces infringes upon human rights and the nation's security, it shall carry out investigations and take necessary measures.
…
16. It shall, on its own initiative, request a joint session of the House of the Federation and of the House of Peoples' Representatives to take appropriate measures when State authorities are unable to arrest violations of human rights within their jurisdiction. It shall, on the basis of the joint decision of the House, give directives to the concerned State authorities.
… (Art. 55) - Amharic1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት ለፌዴራሉ መንግሥት በተሰጠው ሥልጣን ክልል ሕጐችን ያወጣል፡፡
…
7. የፌዴራል መንግሥት፤ የሀገርና የሕዝብ መከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ኃይል አደረጃጀት ይወስናል፡፡ በሥራ አፈጻጸም ረገድ የሚታዩ መሠረታዊ የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶችና የሀገርን ደህንነት የሚነኩ ጉዳዮች ሲከሰቱ ያጣራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፡፡
…
16. በማንኛውም ክልል ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱና ክልሉ ድርጊቱን ማቆም ሳይችል ሲቀር፤ በራሱ አነሳሽነትና ያለክልሉ ፈቃድ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ጥያቄ ያቀርባል፤ በተደረሰበት ውሳኔ መሰረት ለክልሉ ምክር ቤት መመሪያ ይሰጣል፡፡
… (አንቀጽ 55)