SEARCH DATABASE
The Global Gender Equality Constitutional Database is a repository of gender equality related provisions in 194 constitutions from around the world. The Database was updated in partnership with the International Bar Association's Human Rights Institute (IBAHRI) and with support from the Swedish International Development Agency (SIDA) and the Government of Japan. Experience its wealth and depth of information by starting your search now.
Affirmative Action (Broadly)
- English…
3. The historical legacy of inequality and discrimination suffered by women in Ethiopia taken into account, women, in order to remedy this legacy, are entitled to affirmative measures. The purpose of such measures shall be to provide special attention to women so as to enable them to compete and participate on the basis of equality with men in political, social and economic life as well as in public and private institutions.
… (Art. 35) - Amharic…
3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
… (አንቀጽ 35)
Citizenship and Nationality
- English
1. The House of Peoples' Representatives shall have the power of legislation in all matters assigned by this Constitution to Federal jurisdiction.
2. Consistent with the provision of sub-Article 1 of this Article, the House of Peoples' Representatives shall enact specific laws on the following matters:
…
e. Nationality,
… (Art. 55) - Amharic
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት ለፌዴራሉ መንግሥት በተሰጠው የሥልጣን ክልል ሕጐችን ያወጣል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ሕግ ያወጣል፤
…
ሠ/ የዜግነት መብትን፤
… (አንቀጽ 55)
Citizenship and Nationality
- English1. No Ethiopian national shall be deprived of his or her Ethiopian nationality against his or her will. Marriage of an Ethiopian national of either sex to a foreign national shall not annul his or her Ethiopian nationality.
2. Every Ethiopian national has the right to the enjoyment of all rights, protection and benefits derived from Ethiopian nationality as prescribed by law.
3. Any national has the right to change his Ethiopian nationality.
4. Ethiopian nationality may be conferred upon foreigners in accordance with law enacted and procedures established consistent with international agreements ratified by Ethiopia. (Art. 33) - Amharic1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት ከፈቃዱ/ከፈቃዷ ውጭ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን/ዜግነትዋን ሊገፈፍ ወይም ልትገፈፍ አይችልም/አትችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ / ኢትዮጵያዊት ዜጋ ከሌላ ሀገር ዜጋ ጋር የሚፈጽመው/የምጽትፈጽመው ጋብቻ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን / ዜግነትዋን አያስቀርም፡፡
2. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ የሚያስገኘውን መብት ጥበቃና ጥቅም የማግኘት መብት አለው፡፡
3. ማንኛውም ዜጋ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የመለወጥ መብት አለው፡፡
4. ኢትዮጵያ ከአጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር በማይቃረን መንገድ በሚወጣ ሕግ እና በሚደነገግ ሥርዓት መሰረት የኢትዮጵያ ዜግነት ለውጭ ሀገር ሰዎች ሊሰጥ ይችላል፡፡ (አንቀጽ 33)
Citizenship and Nationality
- English1. Any person of either sex shall be an Ethiopian national where both or either parent is Ethiopian.
2. Foreign nationals may acquire Ethiopian nationality.
3. Particulars relating to nationality shall be determined by law. (Art. 6) - Amharic1. ወላጆቹ/ወላጆቿ ወይም ከወላጆቹ/ከወላጆቿ አንደኛቸው ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት የሆነ/የሆነች የኢትዮጵያ ዜጋ ነው/ናት፡፡
2. የውጭ ሀገር ዜጐች የኢትዮጵያ ዜግነት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
3. ዜግነትን በሚመለከት ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡ (አንቀጽ 6)
Education
- English1. To the extent the country's resources permit, policies shall aim to provide all Ethiopians access to … education, …
2. Education shall be provided in a manner that is free from any religious influence, political partisanship or cultural prejudices. (Art. 90) - Amharic1. የሀየሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ … እንዲኖረው ይደረጋል፡፡
2. ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተፅእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሔድ አለበት፡፡ (አንቀጽ 90)
Employment Rights and Protection
- English…
d. Women workers have the right to equal pay for equal work.
2. Workers have the right to reasonable limitation of working hours, to rest, to leisure, to periodic leaves with pay, to remuneration for public holidays as well as healthy and safe work environment.
… (Art. 42) - Amharic…
መ/ሴቶች ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡
2. ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማና አደጋ የማያደረስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው፡፡
… (አንቀጽ 42)
Employment Rights and Protection
- English1. Every Ethiopian has the right to engage freely in economic activity and to pursue a livelihood of his choice anywhere within the national territory.
2. Every Ethiopian has the right to choose his or her means of livelihood, occupation and profession.
…
7. The State shall undertake all measures necessary to increase opportunities for citizens to find gainful employment.
… (Art. 41) - Amharic1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራትና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት አለው፡፡
2. ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያውን፣ ሥራውንና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው፡፡
…
7. መንግሥት ዜጐች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡
… (አንቀጽ 41)
Employment Rights and Protection
- English…
5. a. Women have the right to maternity leave with full pay. The duration of maternity leave shall be determined by law taking into account the nature of the work, the health of the mother and the well-being of the child and family.
b. Maternity leave may, in accordance with the provisions of law, include prenatal leave with full pay.
…
8. Women shall have a right to equality in employment, promotion, pay, and the transfer of pension entitlements.
… (Art. 35) - Amharic…
5. ሀ/ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው፡፡ የወሊድ ፈቃድ ርዝመት ሴቷ የምትሠራውን ሥራ ሁኔታ፣የሴቷን ጤንነት፣ የሕጻኑንና የቤተሰቡን ደህንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕግ ይወሰናል፡፡
ለ/ የወሊድ ፈቃድ በሕግ በሚወሰነው መሰረት ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የሚሰጥ የእርግዝና ፈቃድን ሊጨምር ይችላል፡፡
…
8. ሴቶች የቅጥር፣ የሥራ እድገት፣ የእኩል ክፍያና ጡረታን የማስተላለፍ እኩል መብት አላቸው፡፡
… (አንቀጽ 35)
Equality and Non-Discrimination
- English1. Women shall, in the enjoyment of rights and protections provided for by this Constitution, have equal right with men.
…
3. The historical legacy of inequality and discrimination suffered by women in Ethiopia taken into account, women, in order to remedy this legacy, are entitled to affirmative measures. The purpose of such measures shall be to provide special attention to women so as to enable them to compete and participate on the basis of equality with men in political, social and economic life as well as in public and private institutions.
… (Art. 35) - Amharic1. ሴቶች ይህ ሕገ መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
…
3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
… (አንቀጽ 35)
Equality and Non-Discrimination
- EnglishAll persons are equal before the law and are entitled without any discrimination to the equal protection of the law. In this respect, the law shall guarantee to all persons equal and effective protection without discrimination on grounds of race, nation, nationality, or other social origin, colour, sex, language, religion, political or other opinion, property, birth or other status. (Art. 25)
- Amharicሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ በዘር፣በብሔር፣ ብሔረሰብ፣በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው፡፡ (አንቀጽ 25)