SEARCH DATABASE
The Global Gender Equality Constitutional Database is a repository of gender equality related provisions in 194 constitutions from around the world. The Database was updated in partnership with the International Bar Association's Human Rights Institute (IBAHRI) and with support from the Swedish International Development Agency (SIDA) and the Government of Japan. Experience its wealth and depth of information by starting your search now.
Equality and Non-Discrimination
- English
All persons are equal before the law and are entitled without any discrimination to the equal protection of the law. In this respect, the law shall guarantee to all persons equal and effective protection without discrimination on grounds of race, nation, nationality, or other social origin, colour, sex, language, religion, political or other opinion, property, birth or other status. (Art. 25)
- Amharic
ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ በዘር፣በብሔር፣ ብሔረሰብ፣በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው፡፡ (አንቀጽ 25)
Equality and Non-Discrimination
- English
1. Women shall, in the enjoyment of rights and protections provided for by this Constitution, have equal right with men.
…
3. The historical legacy of inequality and discrimination suffered by women in Ethiopia taken into account, women, in order to remedy this legacy, are entitled to affirmative measures. The purpose of such measures shall be to provide special attention to women so as to enable them to compete and participate on the basis of equality with men in political, social and economic life as well as in public and private institutions.
… (Art. 35) - Amharic
1. ሴቶች ይህ ሕገ መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
…
3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
… (አንቀጽ 35)
Indigenous Peoples
- English
1. Every Nation, Nationality and People in Ethiopia has an unconditional right to self-determination, including the right to secession.
2. Every Nation, Nationality and People in Ethiopia has the right to speak, to write and to develop its own language; to express, to develop and to promote its culture; and to preserve its history.
3. Every Nation, Nationality and People in Ethiopia has the right to a full measure of self-government which includes the right to establish institutions of government in the territory that it inhabits and to equitable representation in state and Federal governments.
…
5. A "Nation, Nationality or People" for the purpose of this Constitution, is a group of people who have or share a large measure of a common culture or similar customs, mutual intelligibility of language, belief in a common or related identities, a common psychological make-up, and who inhabit an identifiable, predominantly contiguous territory. (Art. 39) - Amharic
1. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው፡፡
2. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ በቋንቋው የመናገር፣ የመጻፍ፣ቋንቋውን የማሳደግ እና ባሕሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው፡፡
3. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው፡፡ ይህ መብት ብሔሩ፣ ብሔረሰቡ፣ ሕዝቡ በሰፈረበት መልክዓ ምድር ራሱን የሚያስተዳድርበት መንግሥታዊ ተቋማት የማቋቋም እንዲሁም በክልልና በፌዴራል አስተዳደሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብትን ያጠቃልላል፡፡
…
5. በዚህ ሕገ መንግሥት ውስጥ «ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸውን ባህርይ የሚያሳይ ማኅበረሰብ ነው፡፡ ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባሕል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው፡፡ (አንቀጽ 39)
Indigenous Peoples
- English
…
5. Ethiopian pastoralists have the right to free land for grazing and cultivation as well as the right not to be displaced from their own lands. The implementation shall be specified by law.
… (Art. 40) - Amharic
…
5. የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነጻ የማግኘት፣የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል፡፡
… (አንቀጽ 40)
Indigenous Peoples
- English
…
8. Ethiopian farmers and pastoralists have the right to receive fair prices for their products, that would lead to improvement in their conditions of life and to enable them to obtain an equitable share of the national wealth commensurate with their contribution. This objective shall guide the State in the formulation of economic, social and development policies.
… (Art. 41) - Amharic
…
8. ገበሬዎችና ዘላን ኢትዮጵውያን በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ኑሮ ለመኖር የሚያስችላቸውና ለምርት ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ተገቢ ዋጋ ለምርት ውጤቶቻቸው የማግኘት መብት አላቸው፡፡ መንግሥት የኢኮኖሚ፣የማኅበራዊና የልማት ፖሊሲዎችን በሚተልምበት ጊዜ በዚህ ዓላማ መመራት አለበት፡፡
… (አንቀጽ 41)
Indigenous Peoples
- English
…
2. Members of the House shall be elected from candidates in each electoral district by a plurality of the votes cast. Provisions shall be made by law for special representation for minority Nationalities and Peoples.
3. Members of the House, on the basis of population and special representation of minority Nationalities and Peoples, shall not exceed 550; of these, minority Nationalities and Peoples shall have at least 20 seats. Particulars shall be determined by law.
… (Art. 54) - Amharic
…
2. የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የተለየ ውክልና ያሰፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ይሆናሉ፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
3. የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው አናሳ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ 550 የማይበልጥ ሆኖ ከዚህ ውስጥ አናሳ ብሔረሰቦች 20 የማያንስ መቀመጫ ይኖራቸዋል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይደነግጋል፡፡
… (አንቀጽ 54)
Indigenous Peoples
- English
…
2. Each Nation, Nationality and People shall be represented in the House of the Federation by at least one member. Each Nation or Nationality shall be represented by one additional representative for each one million of its population.
… (Art. 61) - Amharic
…
2. እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ቢያንስ አንድ ተወካይ ይኖረዋል፤በተጨማሪም የብሔር ወይም ብሔረሰቡ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ተጨማሪ ወኪል ይኖረዋል፡፡
… (አንቀጽ 61)
Limitations and/or Derogations
- English
…
2. Everyone has the right to the free development of his personality in a manner compatible with the rights of other citizens.
… (Art. 24) - Amharic
…
2. ማንኛውም ሰው የራሱን ስብዕና ከሌሎች ዜጐች መብቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በነጻ የማሳደግ መብት አለው፡፡
… (አንቀጽ 24)
Limitations and/or Derogations
- English
…
4. a. When a state of emergency is declared, the Council of Ministers shall, in accordance with regulations it issues, have all necessary power to protect the country's peace and sovereignty, and to maintain public security, law and order.
b. The Council of Ministers shall have the power to suspend such political and democratic rights contained in this Constitution to the extent necessary to avert the conditions that required the declaration of a state of emergency.
c. In the exercise of its emergency powers the Council of Ministers cannot, however, suspend or limit the rights provided for in Articles 1, 18, 25, and sub-Articles 1 and 2 of Article 39 of this Constitution.
5. The House of Peoples' Representatives, while declaring a state of emergency, shall simultaneously establish a State of Emergency Inquiry Board, comprising of seven persons to be chosen and assigned by the House from among its members and from legal experts.
6. The State of Emergency Inquiry Board shall have the following powers and responsibilities:
a. To make public within one month the names of all individuals arrested on account of the state of emergency together with the reasons for their arrest.
b. To inspect and follow up that no measure taken during the state of emergency is inhumane.
c. To recommend to the Prime Minister or to the Council of Ministers corrective measures if it finds any case of inhumane treatment.
d. To ensure the prosecution of perpetrators of inhumane acts.
e. To submit its views to the House of Peoples' Representatives on a request to extend the duration of the state of emergency. (Art. 93) - Amharic
…
4. ሀ/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣቸው ደንቦች መሰረት የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብን ደህንነት፣ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
ለ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ የፖለቲካና የዴሞክራሲ መብቶችን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘውደረጃ፣ እስከ ማገድ ሊደርስ የሚችል ነው፡፡
ሐ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥራ የሚያወጣቸው ድንጋጌዎችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ በዚህ ሕገመንግሥት አንቀጽ 1፣፣ 18፣ 25፣ እና 39 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተቀመጡትን መብቶች የሚገድቡ ሊሆኑ አይችሉም፡፡
5. በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላቱና ከሕግ ባለሙያዎች መርጦ የሚመድባቸው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ያቋቁማል፡፡ ቦርዱ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚጸድቅበት ጊዜ ይቋቋማል፣
6. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነቶች አሉት፡፡
ሀ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩትን ግለሰቦች ስም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ ማድረግና የታሰሩበትን ምክንያት መግለጽ፣
ለ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሚወሰዱት እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ ኢሰብዓዊ አለመሆናቸውን መቆጣጠርና መከታተል፣
ሐ/ ማናቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ ኢሰብዓዊ መሆኑን ሲያምንበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የሚኒስሮች ምክር ቤት እርምጃውን እንዲያስተካክል ሐሳብ መስጠት፣
መ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃዎች ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙትን ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ፣
ሠ/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቀጥል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ሲቀርብ ያለውን አስተያየት ለምክር ቤቱ ማቅረብ፡፡ (አንቀጽ 93)
Marriage and Family Life
- English
1. Men and women, without any distinction as to race, nation, nationality or religion, who have attained marriageable age as defined by law, have the right to marry and found a family. They have equal rights while entering into, during marriage and at the time of divorce. Laws shall be enacted to ensure the protection of rights and interests of children at the time of divorce.
2. Marriage shall be entered into only with the free and full consent of the intending spouses.
3. The family is the natural and fundamental unit of society and is entitled to protection by society and the State.
4. In accordance with provisions to be specified by law, a law giving recognition to marriage concluded under systems of religious or customary laws may be enacted.
5. This Constitution shall not preclude the adjudication of disputes relating to personal and family laws in accordance with religious or customary laws, with the consent of the parties to the dispute. Particulars shall be determined by law. (Art. 34) - Amharic
1. በሕግ ከተወሰነው የጋብቻ ዕድሜ የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር፣ በብሔር፣በብሔረሰብ ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው የማግባትና ቤተሰብ የመመስረት መብት አላቸው፡፡ በጋብቻ አፈጻጸም፣ በጋብቻው ዘመንና በፍቺ ጊዜ እኩል መብት አላቸው፡፡ በፍቺም ጊዜ የልጆችን መብትና ጥቅም እንዲከበር የሚያደርጉ ድንጋጌዎች ይደነገጋሉ፡፡
2. ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሰረታል፡፡
3. ቤተሰብ የኅብረተሰብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ ነው፡፡ ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
4. በሕግ በተለይ በሚዘረዘረው መሰረት በሃይማኖት፣ በባሕል የሕግ ሥርዓቶች ላይ ተመስርትው ለሚፈጸሙ ጋብቻዎች እውቅና የሚሰጥ ሕግ ሊወጣ ይችላል፡፡
5. ይህ ሕገ መንግሥት የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሃይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጐች መሰረት መዳኘትን አይከለክልም፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡ (አንቀጽ 34)