SEARCH DATABASE
The Global Gender Equality Constitutional Database is a repository of gender equality related provisions in 194 constitutions from around the world. The Database was updated in partnership with the International Bar Association's Human Rights Institute (IBAHRI) and with support from the Swedish International Development Agency (SIDA) and the Government of Japan. Experience its wealth and depth of information by starting your search now.
ABOUT 74 RESULTS
Marriage and Family Life
Ethiopia
- English…
2. Women have equal rights with men in marriage as prescribed by this Constitution.
…
5. a. Women have the right to maternity leave with full pay. The duration of maternity leave shall be determined by law taking into account the nature of the work, the health of the mother and the well-being of the child and family.
b. Maternity leave may, in accordance with the provisions of law, include prenatal leave with full pay.
…
9. To prevent harm arising from pregnancy and childbirth and in order to safeguard their health, women have the right of access to family planning education, information and capacity. (Art. 35) - Amharic…
2. ሴቶች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
…
5. ሀ/ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው፡፡ የወሊድ ፈቃድ ርዝመት ሴቷ የምትሠራውን ሥራ ሁኔታ፣የሴቷን ጤንነት፣ የሕጻኑንና የቤተሰቡን ደህንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕግ ይወሰናል፡፡
ለ/ የወሊድ ፈቃድ በሕግ በሚወሰነው መሰረት ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የሚሰጥ የእርግዝና ፈቃድን ሊጨምር ይችላል፡፡
…
9. ሴቶች በእርግዝናና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከልና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣ መረጃ እና አቅም የማግኘት መብት አላቸው፡፡ (አንቀጽ 35)
Marriage and Family Life
Ethiopia
- English1. Men and women, without any distinction as to race, nation, nationality or religion, who have attained marriageable age as defined by law, have the right to marry and found a family. They have equal rights while entering into, during marriage and at the time of divorce. Laws shall be enacted to ensure the protection of rights and interests of children at the time of divorce.
2. Marriage shall be entered into only with the free and full consent of the intending spouses.
3. The family is the natural and fundamental unit of society and is entitled to protection by society and the State.
4. In accordance with provisions to be specified by law, a law giving recognition to marriage concluded under systems of religious or customary laws may be enacted.
5. This Constitution shall not preclude the adjudication of disputes relating to personal and family laws in accordance with religious or customary laws, with the consent of the parties to the dispute. Particulars shall be determined by law. (Art. 34) - Amharic1. በሕግ ከተወሰነው የጋብቻ ዕድሜ የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር፣ በብሔር፣በብሔረሰብ ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው የማግባትና ቤተሰብ የመመስረት መብት አላቸው፡፡ በጋብቻ አፈጻጸም፣ በጋብቻው ዘመንና በፍቺ ጊዜ እኩል መብት አላቸው፡፡ በፍቺም ጊዜ የልጆችን መብትና ጥቅም እንዲከበር የሚያደርጉ ድንጋጌዎች ይደነገጋሉ፡፡
2. ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሰረታል፡፡
3. ቤተሰብ የኅብረተሰብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ ነው፡፡ ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
4. በሕግ በተለይ በሚዘረዘረው መሰረት በሃይማኖት፣ በባሕል የሕግ ሥርዓቶች ላይ ተመስርትው ለሚፈጸሙ ጋብቻዎች እውቅና የሚሰጥ ሕግ ሊወጣ ይችላል፡፡
5. ይህ ሕገ መንግሥት የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሃይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጐች መሰረት መዳኘትን አይከለክልም፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡ (አንቀጽ 34)
Minorities
Ethiopia
- English…
2. Members of the House shall be elected from candidates in each electoral district by a plurality of the votes cast. Provisions shall be made by law for special representation for minority Nationalities and Peoples.
3. Members of the House, on the basis of population and special representation of minority Nationalities and Peoples, shall not exceed 550; of these, minority Nationalities and Peoples shall have at least 20 seats. Particulars shall be determined by law.
… (Art. 54) - Amharic…
2. የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የተለየ ውክልና ያሰፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ይሆናሉ፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
3. የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው አናሳ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ 550 የማይበልጥ ሆኖ ከዚህ ውስጥ አናሳ ብሔረሰቦች 20 የማያንስ መቀመጫ ይኖራቸዋል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይደነግጋል፡፡
… (አንቀጽ 54)
Participation in Public Life and Institutions
Ethiopia
- English…
7. Government shall ensure the participation of women in equality with men in all economic and social development endeavors.
… (Art. 89) - Amharic…
7. መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት፡፡
… (አንቀጽ 89)
Participation in Public Life and Institutions
Ethiopia
- English1. Every Ethiopian national without any discrimination based on colour, race, nation, nationality, sex, language, religion, political or other opinion or other status, has the following rights:
a. to take part in the conduct of public affairs, directly and through freely chosen representatives;
… (Art. 38) - Amharic1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለከካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት የሚከተሉት መብቶች አሉት፤
ሀ/ በቀጥታ እና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በሕዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ፣
… (አንቀጽ 38)
Participation in Public Life and Institutions
Ethiopia
- English…
3. The historical legacy of inequality and discrimination suffered by women in Ethiopia taken into account, women, in order to remedy this legacy, are entitled to affirmative measures. The purpose of such measures shall be to provide special attention to women so as to enable them to compete and participate on the basis of equality with men in political, social and economic life as well as in public and private institutions.
…
6. Women have the right to full consultation in the formulation of national development policies, the designing and execution of projects, and particularly in the case of projects affecting the interests of women.
… (Art. 35) - Amharic…
3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
…
6. ሴቶች በብሔራዊ የልማት ፖሊሲዎች ዕቅድና በኘሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም፣በተለይ የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ኘሮጀክቶች ሐሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው፡፡
… (አንቀጽ 35)
Property, Inheritance and Land Tenure
Ethiopia
- English1. Every Ethiopian citizen has the right to the ownership of private property. Unless prescribed otherwise by law on account of public interest, this right shall include the right to acquire, to use and, in a manner compatible with the rights of other citizens, to dispose of such property by sale or bequest or to transfer it otherwise.
2. "Private property", for the purpose of this Article, shall mean any tangible or intangible product which has value and is produced by the labour, creativity, enterprise or capital of an individual citizen, associations which enjoy juridical personality under the law, or in appropriate circumstances, by communities specifically empowered by law to own property in common.
3. The right to ownership of rural and urban land, as well as of all natural resources, is exclusively vested in the State and in the peoples of Ethiopia. Land is a common property of the Nations, Nationalities and Peoples of Ethiopia and shall not be subject to sale or to other means of exchange.
4. Ethiopian peasants have right to obtain land without payment and the protection against eviction from their possession. The implementation of this provision shall be specified by law.
5. Ethiopian pastoralists have the right to free land for grazing and cultivation as well as the right not to be displaced from their own lands. The implementation shall be specified by law.
…
7. Every Ethiopian shall have the full right to the immovable property he builds and to the permanent improvements he brings about on the land by his labour or capital. This right shall include the right to alienate, to bequeath, and, where the right of use expires, to remove his property, transfer his title, or claim compensation for it. Particulars shall be determined by law.
… (Art. 40) - Amharic1. ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ ይከበርላታል፡፡ ይህ መብት የሕዝብን ጥቅም ለመጠበቅ በሌላ ሁኔታ በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም ወይም የሌሎችን ዜጐች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረትን የመሸጥ የማውረስ ወይም በሌላ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን ያካትታል፡፡
2. ለዚህ አንቀጽ ዓላማ «የግል ንብረት» ማለት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ሕጋዊ ሰውነት በሕግ የተሰጣቸው ኢትዮጵያዊ ማኅበራት ወይም አግባብ በአላቸው ሁኔታዎች በሕግ በተለየ በጋራ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የተፈቀደላቸው ማኅበረሰቦች በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ተጨባጭ የሆነና የተጨባጭነት ጠባይ ሳይኖረው ዋጋ ያለው ውጤት ነው፡፡
3. የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው፡፡
4. የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው፡፡ አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ይወጣል፡፡
5. የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነጻ የማግኘት፣የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል፡፡
…
7. ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ፣ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው፡፡ ይህ መብት የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ የመሬት ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን የማንሳት፣ ባለቤትነቱን የማዛወር ወይም የካሳ ክፍያ የመጠየቅ መብትን ያካትታል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል፡፡
… (አንቀጽ 40)
Property, Inheritance and Land Tenure
Ethiopia
- English…
7. Women have the right to acquire, administer, control, use and transfer property. In particular, they have equal rights with men with respect to use, transfer, administration and control of land. They shall also enjoy equal treatment in the inheritance of property.
… (Art. 35) - Amharic…
7. ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብት አላቸው፡፡ በተለይም መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡ እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት አላቸው፡፡
… (አንቀጽ 35)
Protection from Violence
Ethiopia
- English1. Everyone has the right to protection against cruel, inhuman or degrading treatment or punishment.
2. No one shall be held in slavery or servitude. Trafficking in human beings for whatever purpose is prohibited.
3. No one shall be required to perform forced or compulsory labour.
… (Art. 18) - Amharic1. ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡
2. ማንኛውም ሰው በባርነት ወይም በግዴታ አገልጋይነት ሊያዝ አይችልም፡፡ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው፡፡
3. ማንኛውም ሰው በኃይል ተገዶ ወይም ግዴታ ለማሟላት ማንኛውንም ሥራ እንዲሠራ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡
… (አንቀጽ 18)
Protection from Violence
Ethiopia
- EnglishEveryone has the right to protection against bodily harm. (Art. 16)
- Amharicማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፡፡ (አንቀጽ 16)